በብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ማሻሻያ ዙሪያ የዉይይት መድረክ ተካሄደ

ጥር 26/2015 ዓ.ም – አዲስ አበባ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር በብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ማሻሻያ ዙሪያ ልዩ ትኩረት ከሚሹ ወጣቶች (አካል ጉዳተኛ ወጣቶች፣ የጎዳና ተዳዳሪ ወጣቶች፣ በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወጣቶች፣ እንዲሁም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሴት ወጣቶች) ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡
በመድረኩ በመገኘት ያወያዩት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሙና አህመድ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም ተቀርፆ ሲተገበር የቆየው ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ልዩ ትኩረት የሚሹ ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን በሚፈለገው መልኩ ያላረጋገጠ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በቀጣይ እነዚህ ወጣቶች በመደራጀት መብትና ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው በመግለጽ የሚሻሻለው ፖሊሲ የሀገራችንን ወጣቶች አንገብጋቢ ችግሮችና ጉዳዮችን የሚዳሰስ እንደሚሆንና ልዩ ትኩረት የሚሹ ወጣቶች ጉዳዮችን በተገቢው በመዳሰስ አካታች እና አሳታፊ ሆኖ እንደሚቀረጽ፣ ለአፈጻጸሚም ተገቢው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡
በመድረኩ ዝርዝር ሀሳቦች ከተሳታፊዎች የቀረቡ ሲሆን በሚሻሻለው ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ የአካል ጉዳተኛ ወጣቶች፣ የጎዳና ተዳዳሪ ወጣቶች፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሴት ወጣቶች እንዲሁም በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ጉዳዮች ለአብነትም የትምህርትና የስልጠና ተሳትፎ፣ የጤና ተጠቃሚነት፣ የስብዕና ግንባታ፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና ሌሎች ማህበራዊ ተጠቃሚነቶች መካተት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
የፖሊሲ ማሻሻያ ቡድን አባላት በበኩላቸው ለፖሊሲ ማሻሻያ የሚሆኑ ጠቃሚ ሀሳቦች የተነሱ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ግብዓቶቹ በሚሻሻለው ፖሊሲ ውስጥ ተካተው ልዩ ትኩረት የሚሹ ወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ፖሊሲው እንደሚቃኝ ገልጸዋል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *