ድንበር ተሻጋሪ የሴቶች ግርዛትን በተመለከተ በሱማሌ ክልልና በሱማሌ ላንድ በተካሄደው ጥናት እና በተሞክሮ ልውውጥ ምክክር ተካሄደ

Cross boarder FGM በተመለከተ በጅግጅጋ ከተማ የሁለቱም ሀገራት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር እና የቢሮ የሴቶችና ህጻናት ዘርፍ የስራ ሀላፊዎች ፣የሁለቱም ሀገራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች፣የአጋር አካላት የ GIZ ተወካዮች በተገኙበት በሱማሌ ክልልና በሱማሌ ላንድ በተካሄደው ጥናት እና በተሞክሮ ልውውጥ ላይ ምክክር ተካሄደ።

በዚህ ምክክር መድረክ በኢትዮጲያ፣ሱዳን፣ጂቡቲ እና ሱማሌ በሴት ልጆች ላይ የሚፈጸመውን ግርዛት ለማስቆም በሚተገብረው GIZ ፕሮጀክት አማካኝነት በኢትዮጲያና በሱማሌ ክልል ድንበር ቦታዎች ላይ በሁለቱም ሀገራት ዩኒቨርስቲዎች የተጠኑት ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተካሄዶባቸው የጥናቱ ምክረ ሃሳቦች መሰረት ያደረጉ በቀጣይ በጋራ ሊሰሩ የሚችሉ ስራዎች ተለይተው መነሻ እቅድ እንደዘጋጅ ተደርጋል ፤፤ ከዚህ በተጨማሪ Mombasa declaration በተመለከተ በኬንያ፣ሁጋንዳ፣ኢትዮጲያ ፣ሱማሌ መካካል Cross boarder FGM በተመለከተ የተደረገው ስምምነት አስመልክቶና ስምምነቱን አፈጻጸም በተመለከተ ተደርገው የነበሩ ምክክሮች ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎች በሚኒስትር መ/ቤቱ በኩል በአቶ ስለሺ ታደሰ በኩል እንዲቀርብ ተደርጎ ውይይት ተካሂዶባቸው cross boarder initiative ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር በዚህ አካባቢ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታችና ስምምነት በተደረሰባቸው በቀጣይ መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥቶት ከተሰራ ውጤት ሊመጣና ለሌሎቹም ቦታዎች ተሞክሮ ሊሆን እንደሚችል የጋራ ስምምነት ተደርሶበታል

በቀጣይ ፕሮግራም የፕሮጀክቱ ትግበራ በተመለከተ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ያዘጋጁትን ድራማ ተሳታፊዎችና ተማሪዎች በተገኙበት የታየና ከዚህ በተጨማሪ በGIZ በኩል ድጋፍ ተደርጎላቸው በማህበረሰቡ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ያከናወናቸው ስራዎችና ተሞክሮዎች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *