የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ” ማህበራዊ ጥበቃ ለሃገር ግንባታ” በሚል መሪ ቃል የሚያካሂደውን አገር አቀፍ ኮንፍረንስ አስመልክቶ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ኮንፈረንሱን በማስመልከት ለሚዲያዎች በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ከግንቦት 15-16 አፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የሚያካሂደው ይህ አገር አቀፍ ኮንፈረንስ የማህበራዊ ጥበቃ ኘሮግራሞችን አተገባበር እና ስርዓትን የተመለከቱ አገራዊና የውጪ አገራት ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በከፋ ድኅነት ውስጥ ለሚገኙና ለማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከሚያከናውናቸው ሥራዎች አንድ መሆኑን ገልፀዋል።

የማህበራዊ ጥበቃ ሥርዓት አስፈላጊነትና ጠቀሜታን ማስገንዘብ ዓለማቀፋዊና አህጉራዊ ልምዶችን መዳሰስ ፣ የተሻለ እና ጥራት ያለው የማህበራዊ ጥበቃ ፓሊሲ እና ስትራቴጂ ለመቀየስ ግብዓቶች የሚገኙበት እንደሆነ ጠቁመዋል።

ከ 500 በላይ የአገር ውስጥ እና የውጪ አገራት ተሳታፊዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *