በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በጋራ መከላከል ይገባል ተባለ።

(ግንቦት 27/2015)
በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለመከላከል እንደ ሀገር የማህበረሰቡ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።በእለቱ ከክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለመከላከል በክልሎች እየተከናወኑ ያሉ የፍትህና ፣የጤና እንዲሁም ማህበራዊ ድጋፍ አሰጣጥ ልምድ ልውውጥ በማከናወን ላይ ይገኛል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ሕፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ አገር አቀፍ የጾታዊ ጥቃት መከላከልና ምላሽ ሥራዎችን ክልሎች በተቀናጀ መልኩ ሊያከናውኑ ይገባል ብለዋል።

ሴቶችና ሕፃናት ከጥቃት ነፃ ሆነው በትምህርት በአመራርነት በኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ መረባረብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በመድረኩ የፌደራልና የክልል የሴቶችና ማህበራዊ፤የጤናና የፍትህ ዘርፍ የተገኙ ሲሆን ሁሉም ሪፓርት በማቅረብና በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እየተዘጋጁ ያሉ High level intitative የሆኑ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መከላከል እና ምላሽ መስጠት ፖሊሲ፥የጉዳይ አያያ ዝcase managnment ፤የአገልግሎት ምላሽ አስጣጥ ስታንዳርድና የፆታ ጥቃት አድራሾች ምዝገባ ስርአት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ።

በመጨረሻም በመርሃ ግብሩ ሰፊ የውይይት ሀሳብ ተነስቶ ግብአትና የቀጣይ አቅጣጫ ተይዞ መድረኩ ተጠናቋል።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *