ህፃናትና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደህንነት ላይ ያተኮረ የፖናል ውይይት ተካሄደ

(አዲስ አበባ፣ ሰኔ 03/2015 ዓ.ም) የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ የሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ከቻይልድ ፈንድ ጋር በመተባበር ህፃናትና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደህንነት ላይ ያተኮረ የፖናል ውይይት ተካሄደ በዛሬው ዕለት ተካሄደ።
የአፍሪካ ህፃናት ቀን በአፍሪካ ለ33ኛ በአገራችን ለ 32ኛ ጊዜ በተለያዩ ክንውኖች በመከበር ላይ ይገኛል።
በዓሉ በአፍሪካ ደረጃ ‘The rights of child in the digital environment” በአገራችን ደግሞ “ፍቅር ሰላም እንክብካቤ እና ጥበቃ ለሁሉም ህፃናት!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን በፖናል ውይይቱ ላይ የመክፈቻ መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃነናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ የህፃናት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት በአገራችን እያደገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የማህበራዊ ሚዲያና የኢንተርኔት ተጠቃሚነትታቸው ለጤና ችግሮችና ለተለያዩ ጥቃቶችም ተጋላጭ ያደርጋቸዋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ህፃናት የዲጂታሉን ዓለም ሲጠቀሙ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ወላጆችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻና አጋር አካላትም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው በቅንጅት እንዲሰሩ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ ጥሪ አቅርበዋል።
በፓናል ውይይቱ ላይ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከመረጃ መረብ ደህንነት፣ ከፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት፣ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አካላት እንዲሁም የኢትዮጵያ ህጻናት ፓርላማ ፕሬዝዳንት ተሳትፈውበታል።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ የህፃናት ፖርላማ ተወካዮች፣ መምህራና ወላጆች ተገኝተዋል።
ዲጂታል ቴክኖሎጂ ህፃናት በትምህርት፣ እራስን ለመግለፅና ከተቀረው ዓለም ጋር ቅርብ በመሆን መብቶቻቸውን እንዲያስጠብቁ የማድረግ በጎ ጎን እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ክትትልና ጥበቃ ሊደረግበት እንደሚገባል በውይይቱ አጽዕኖት ተሰጥቶታል።
Please follow and like us: