በጃፓን መንግስት ትብብር የሴቶች ማረፊያ ማዕከል ለማቋቋም የሚያስችል መሰረተ ድንጋይ በሴቶች ማረፊያና ልማት ማህበር(AWSAD) ቅጥር ግቢ ውስጥ ተቀመጠ፡፡

በጃፓን መንግስት ትብብር የሴቶች ማረፊያ ማዕከል ለማቋቋም የሚያስችል መሰረተ ድንጋይ በሴቶች ማረፊያና ልማት ማህበር(AWSAD) ቅጥር ግቢ ውስጥ ተቀመጠ፡፡


(ህዳር 6/2016) የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተርና በኢትጵያ የጃፓን አምባሳደር ታኮ ኢቶ እንዲሁም የፖርቹጋል ፣ የጀርመንና የፊንላንድ አማባሳደሮች በተገኙበት በጋራ በመሆን ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ማረፊያ ማዕከል የሚሆን የሴቶች ማረፊያና ልማት ማህበር(AWSAD) ለማቋቋም የሚሆን መሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

በዕለቱ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናጽ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ እንደገለፁት በቅርብ ግዜ የ16ቱ ጾታዊ ጥቃት የመከላከል ቀናትን በተመለከተ ከሴት አምባሳደሮች ጋር በተደረገው ውይይት ከመንግስት በተጨማሪ የሴቶች ማረፊያ ማእከላት ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች እና ታዳጊ ሴቶች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተቋቁመው፣ የህግ፣ የምክር፣ የህክምናና የስነልቦናና፣ የክህሎት ሙያ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ድጋፍ መደረግ እንዳለበት ስምነነት ላይ መደረሱን አስታውሰው የጃፓን መንግስት ማእከሉን ለማቋቋም የወሰነው ውሳኔ ምላሽ ተደርጎ እንደሚወሰድ በመግለጽ ይህንንም ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ እውቅና እንደሚሰጠው ገልፀዋል፡፡

ሚንስትራ አክለውም ሚኒስትር መስሪያቤቱ ከጾታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ ያለውን አመለካከት ለመለወጥ የሚያስችሉ የግንዛቤ፣የንቅናቄ፣ጥቃት መከላከልና ምላሽ አሰጣጥ ለማጎልበት ከባለድርሻና አጋር አካላት ግር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሴቶች ማረፊያና ልማት ማህበር(AWSAD) መስራችና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ማሪያ ሙኒር በበኩላቸው ማዕከሉ የመኝታ ክፍሎችን ለማቋቋም የኢትጵያና የጃፓን መንግስትን ፣ አለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶችንና እስከዛሬ በበጎ ፍቃድ ያገለገሉ ሰዎችን አመስግነዋል፡፡

Please follow and like us: