ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ጋር የማህበራዊ ጥበቃ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተደረገ።

የአለም የምግብ ፕሮግራም ሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስቴርና ውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በጋራ በመሆን በማህበራዊ ጥበቃ በውሀና መስኖ በትምህርት በዘመናዊ ግብርና ጤና እንዲሁም ሌሎች የሰብአዊ ድጋፎች ዙሪያ በትብብርና በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር የተለያዩ ስምምነቶችን እንደምትፈራረም አስታውሰው ነገር ግን ተደራሽ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ በዘላቂነት መስራቱ ላይ ክፍተት መኖሩን ጠቅሰዋል።

የአለም የምግብ ፕሮግራም በፈጣን የገጠር ትራንስፎርሜሽን (RRT) Rapid Rural Transformation ኘሮጀክት የሚፈለገውን ግብ እስኪመታ ዘላቂነት ባለው መልኩ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል ።

ሚንስትሯ አክለውም የአለም የምግብ ኘሮግራም በኢትዮጵያ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ለተፈናቃዮች ተፈናቃዮችን ለሚያስተናግድ አካባቢዎች ለሚያቀርበው የምግብ እና የገንዘብ ድጋፍም አመስግነዋል።

በፈጣን የገጠር ትራንስፎርሜሽን (RRT) Rapid Rural Transformation ኘሮጀክትም ሴቶች፣ወጣቶች ተፈናቃይ ዜጎችና ተጋላጭና የማህበራዊ ጥበቃአገልግሎትን ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ዋነኛ የትኩረት አካል መሆናቸውንም አድንቀዋል ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ በበኩላቸው በአገሪቱ ውስጥ በርካታ ወንዞችና ሌሎች የውኃ አካላት የውኃ ምንጭ ሆነው ቢገኙም፣ አገሪቱ ሀብቱን ሙሉ በሙሉ ተጠቅማበት አንደማታውቅ ገልፀዋል ።

ይህ ኘሮጀክትም አንድ ህዝብ በውሃና ሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶች ልማት፣አያያዝ እና በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋል ላይ ለሚደርገው ጥረት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም የአለም የምግብ ፕሮግራም በመስኖ እርሻ፣ በተፈጥሮ ሃብት አያያዝ እና በአነስተኛ የስራ ፈጠራ ክህሎት፣የምግብ ዋስትና እንዲኖራቸው ፣ በፀሃይ ኃይል የሚንቀሳቀሱ ማዕከላት ዘላቂ የውሃ ምንጭ እና አይሲቲ በርቀት አካባቢዎች በማቋቋም ለህብረተሰቡ አባላት አስፈላጊ አገልግሎቶችን እንደ ኢነርጂ፣ ውሃ እና ዲጂታል መድረኮችን ማዘጋጀቱን አድንቀዋል ።

የአለም የምግብ ፕሮግራም ኢትዮጵያ ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክትር ክሪስ ኒኮ በበኩላቸው WFP በዚህ የሙከራ ፕሮጄክት የገጠር ትራንስፎርሜሽን በጂኦግራፊያዊ ገለልተኛ አካባቢዎች እንኳን ሳይቀር ለመስኖ አገልግሎት ንፁህ ውሃ በማቅረብ ፣የጤና አጠባበቅ ተቋማትን አሠራር ፣የስራ ፈጣራ ዕድሎችን
እና ለዜጎቿ ምቹ ሀገር እንድትሆን እንደሚያስችላት ጠቁመዋል ።

ዳይሬክተሩ አክለውም የአለም የምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ – በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከፌዴራል እና ከክልል ባለስልጣናት እና ከመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አጋሮች ጋር በመሆን ለተፈናቀሉ እና በግጭት ለተጎዱ ዜጎች የምግብ አቅርቦትን እንደሚያቀርብ ገልፀዋል ።

በፈጣን የገጠር ትራንስፎርሜሽን (RRT) የሙከራ ፕሮጄክት በማዳጋስካር የተጀመረና በኢትዮጵያም አፋር፣ አማራ ፣ ትግራይ፣ በደቡብና ጋምቤላ አካባቢዎች እንደሚስፋፋ ተገልጿል ።

Please follow and like us: