በትግራይ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሠብ ክፍሎች ከ813 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሠብ ክፍሎች ከ813 ሺህ በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 813 ሺህ 629 ብር የሚገመት ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቂሳቁሶችን ለትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጊዜያዊ አስተዳደር የሴቶች ጉዳይ ቢሮ በዛሬው እለት አስረክቧል።

ድጋፉ በአክሱም እና ተምቤን በአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲሁም በመጠለያ እና በማገገሚያ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙና ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶችና ህጻናት ግልጋሎት እንደሚውል ተገልጿል።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የክልሉ የሴቶች ጉዳይ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሪሻን ኪሮስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባደረገው ድጋፍ መደሠታቸውን ገልጸዋል።

ሆኖም የክልሉ የችግር መጠን ሰፊ በመሆኑ ድጋፉ ወደፊትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።ቀደም ሲልም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ልዩ ልዩ ድጋፎችን ማድረጉንና ቀጣይነት እንደሚኖረውም በርክክቡ ወቅት ተገልጿል።

Please follow and like us: