“በሴክተሩ እየታየ ያለውን ጥረትና ጅማሮ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ቅንጅታዊ አሰራር ይበልጥ ማጠናከር ይገባል” ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር)

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሴክተር የ2016 በጀት አመት 6 የስድስት ወር እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።በመድረኩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር)  ባለፉት ስድስት ወራት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶችንና የወጣቶችን እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ብሎም የህፃናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት በቅንጅት መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የአካል ጉዳተኞችን፣ የአረጋውያን እንዲሁም ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን አካታችና ተደራሽ ያደረጉ ሰፊ ስራዎች መስራታቸውን ጠቁመዋል።ሆኖም በሴክተሩ ተደራሽ የሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑንና የዘርፉን የተሻጋሪነት ባህሪ ከግምት ውስጥ በማስገባት ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት በቅንጅት መስራት ወሳኝ እንደሆነ አስምረውበታል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት በየዘርፉ አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ቢሆንም አሁንም በአሰራር የሚስተዋሉ ክፍተቶች፣ ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች፣ ከአመለካከት ጋር የተቆራኙ እንቅፋቶች፤ ከማስፈጸምና ከመፈጸም አቅም ጋር የተያያዙ ውስንነቶች መኖራቸው አንስተዋል።

በተለይ በተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ሳቢያ ለከፋ ችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በአገራችን በመኖራቸው እነዚህን ወገኖች ለመታደግና ዘላቂ አገራዊ መፍትሔ ለማበጀት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል።በሴክተሩ እየታየ ያለውን ጥረትና ጅማሮ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ቅንጅታዊ አሰራር ይበልጥ ማጠናከር ይገባልም ብለዋል።

ጎልተው የወጡ ስኬታማ ልምዶችንና መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋፋት ለላቀ ውጤታማነት በትጋት መስራት እንደሚጠበቅ ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በአጽዕኖት አሳስበዋል፡፡በእለቱም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየለማ ያለውን የእቅድና ሪፓርት መረጃ መለዋወጫ የአሰራር ስርአት(system) ላይ ውይይት ተደርጓል።

በጋራ ጉባኤው ላይ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጋር በጋራና በቅንጅት የሚሰሩ የማህበረሰብ አደረጃጀቶች ተገኝተዋል።
ይህ የአሰራር ስርአት(system) ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር የእቅድና ሪፖርት መረጃ መለዋወጫነት ባሻገር እቅድና ሪፖርት ወቅቱንና ታማኝነቱን ይጨምራል ተብሏል።

Please follow and like us: