በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለማሳለፍ ከፍልሰት ጋር የተያዙ መረጃዎችን ዲጂታይዝ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ተናገሩ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢፌዴሪ የስደተኞችና የተመላሾች አገልግሎት፣ ከአውሮፓ ህብረት እና ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር በዳታ መጋራት ስርዓት እና የሚመለከታቸው በጋራ መስራት በሚቻሉበት ዙሪያ እየመከሩ ነው።

መረጃዎችን በአንድ ቋት ማደራጀት መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል፣ ለወንጀሉ ተጠቂዎች ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ እና መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ያስችላል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ የፍልሰተኞችን መረጃ የማደራጀት ስራ የተጎጂዎችን መብትና ደህንነት ለማስከበርና መረጃን መሰረት የደረገ ውሳኔ ለመስጠት አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ከመረጃ ቋት ግንባታ ጎን ለጎን በመረጃ አመንጪና ተጠቃሚ መካከል የመረጃ ቅብብሎሹን ውጤታማና የተሰላጠ ለማድረግ ይሰራል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ የስደት ተመላሽ ዜጎች መረጃ አያያዝና ልውውጥ ስርዓትን ውጤታማ ለማድረግና ዜጎችን የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ዓለም አቀፍ ችግር ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ወንጀሉን ለመከላከል የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎችን በማውጣት እና አለም አቀፋዊ ስምምነቶችን የአገራችን ህግ አካል በማድረግ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

Please follow and like us: