ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸለሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት፣ በሮም ጣልያን በተሰናዳ ክብረ በዓል የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል።

 

ሽልማቱ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት፣ ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት የተበረከተ ነው።

እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!!

Please follow and like us: