አንጋፋው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት /ኢዜአ/ ያስገነባውን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ አስመርቋል።

ከተመሠረተ 82 ዓመታት የሆነው አንጋፋው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ብሔራዊ መግባባት የመፍጠርና የሀገር ገፅታ ግንባታ ተልዕኮውን ለማሳካት ዜና እና ዜና ነክ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ኢዜአ ባለፉት በርካታ ዓመታት ዜናዎችን፣ መረጃዎችን ከአገር ውስጥ እና ከመላው ዓለም ለህዝብ ተደራሽ ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የአገር ባለውለታ አንጋፋ ተቋም መሆኑንም በስነስርዓቱ ላይ ተጠቁሟል፡፡

ተቋሙ ያስገነባው ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስም በዛሬው እለት በደማቅ ሥነ- ስርዓት ተመርቋል።

 

 

በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤት ክብርተ ሁሪያ አሊ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሚዲያ አመራሮችና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለኢዜአ አመራሮችና ባለሙያዎች መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን ይመኛል።

Please follow and like us: