የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና ዶ/ር ኢንጂነር አምባሳደር ስለሺ በቀለ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርና በአሜሪካ በነበረው ጉብኝት የተከናወኑ ተግባራት ዙርያ ተወያይተዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር  ከልኡካን ቡድናቸው ጋር በጋራ በመሆን አሊያንስ ኬር ናው እና የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጋራ ባዘጋጁት መድረኮችና የጎን ለጎን ውይይቶች የተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡

ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በውይይቱ ከልኡካን ቡድናቸው ጋር ባካሄዱት ውይይቶች አሊያንስ ኬር ናው በኢትዮጵያ ከበጎ ፍቃድ ጋር ተያይዞ ሚለማከናወን ቃል የተገቡ ተግባራት ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

ዶ/ር ኤርጎጌ አክለውም መቀመጫውን ቴክሳስ አሜሪካ ካደረገው በክነር ኢንተርናሽናል ከተባለ ድርጅት ጋር ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች ህፃናትና ሴቶች ማህበራዊ ጥበቃ ላይ የሚሰራውን ስራ ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ዜጎችን  ተጠቃሚ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ የተገኙ ተጨባጭና ፍሬያማ ስምምነቶችን ዳሰዋል፡፡

በተጨማሪም አኩና ኩክ ጋር በጋራ በመሆን ጥቁር ዲያስፖራዎችን የታሪክ ትርክቶች ላይ የሚያተኩሩ ከኢትዮጵያውያን ወጣት ፊልም ባለሙያዎች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያሥችሉቅድመ ሁኔታዎችም ላይ ተወያተዋል፡፡

Please follow and like us: