የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የአየርላንድ ኤምባሲ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡

ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደር ኒኮላ ብሪናን ጋር በጽህፈት ቤታቸው በተወያዩበት ወቅት እንደተገለጸው የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የአየርላንድ ኤምባሲ ድጋፍ እንደሚሰጥ አምባሰደርዋ ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ሚኒስቴር መስራቤቱ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው ከነዚህም አንዱ ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ሚኒስትሯ አክለውም የአየርላንድ መንግስት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለሚሰራው ስራ ለወደፊት በትብብርና በቅንጅት ለመስራት መፈለጉን አድንቀዋል፡፡

 

በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደር ኒኮላ ብሪናን በበኩላቸው መንግስታቸው የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚሰራው ስራ በተጨማሪ ፣የስርዓተ-ፆታ እኩልነት ፣ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ የሚሰጠውን ድጋፍ ከሚኒስቴር መስራቤቱ  ዘርፈ ብዙ  ጉዳዮች ጋር በትብብርና በቅንጅት ለመስራት ዝግጁነቱን አረጋግጠዋል፡፡

Please follow and like us: