ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች እና የአእምሮ ጤና

ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች እና የአእምሮ ጤና

– የታዳጊ ልጆች እድሜ (ጉርምስና) ልዩና ወሳኝ ጊዜ ነው:: አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ለውጦቹም ከፍተኛ ናቸው።

– በዚህ ጊዜ ላይ ለድህነት፣ ለጥቃት (አካላዊም ፆታዊ) መጋለጥ እዚህ ዕድሜ ላይ ላሉ ልጆች ለአእምሮ ጤና መታወክ የበለጠ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል::

አጋላጮች ፦
▫️የአቻ ግፊት
▫️አካባቢያዊ ተጽዕኖዎች
▫️አካላዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት
▫️የቤት ውስጥ ሰላም መጓደል
▫️የማንነት ጥያቄ
▫️የሚዲያ ተጽዕኖ
▫️ከፍላጎት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች የተወሰኑት ናቸው።

– በተለይም የአዕምሮ እድገት ውስንነት፣ የተለያዩ የነርቭ ችግሮች፣ የቅርብ ቤተሰብ ድጋፍ የሌላቸው ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች ደግሞ የበለጠ ለአዕምሮ ጤና መታወክ የተጋለጡ ናቸው።

ከስሜት ጋር የተያያዙ ችግሮች ፦
* ከልክ በላይ ጭንቀት
* የስሜት መዋዠቅ
* ድባቴ፣ ራስን ማግለል አልፎም
* በህይወት_መቆየት_አለመፈልግ

የባህሪ ችግሮች ፦
° ትኩረት ማጣት፣
° ለነገሮች መቸኮል፣
° የፀባይ ለውጥ መኖር

የአመጋገብ ችግር ፦
* ውፍረት እንዳይመጣ ከሚል ከፍተኛ የሆነ የአመጋገብ ችግር የሚመጣ ነው።

የስነ-ልቦና ቀውስ ፦
• ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተሉ ያደርጋል።
• ራሳቸውን በተለያዩ ሱሶች ይጎዳሉ።
• ከማህበረሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከፍተኛ  ተጽዕኖ ያሳድርበታል።

-ታዲያ ይህ እንዳይሆን ምን እናድርግ ?
▪️ቤተሰብ ልጆቹ በሰውነታቸው ላይ ለውጥ እየተካሄደ እንደሆነ በመረዳት ለልጆቹ ከምን ጊዜውም በላይ ቅርብ መሆን አለበት።
▪️ራሳቸውን በተለያዩ ዓይነት ስራዎቸ(እንደ ስፖርት ያሉ ነገሮች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ)፣ የመፍትሄ ሰዎች እንዲሆኑ፣ በጤነኛ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ  በማድረግ ሁሉም ሰው የድርሻውን ማድረግ አለበት።

በመላኩ ባዩ

ምንጭ፦ የአለም ጤና ድርጅት

Please follow and like us: