ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ ለ40 ሺህ አረጋውያን የዓይን ህክምና በተለያዩ ክልሎች ይሰጣል

ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 28 በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች ለ40 ሺህ አረጋውያን ነፃ የዓይን ህክምና መሰጠቱን አስመልክቶ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና አልባሳር ዓለም አቀፍ ፋውንዴሽን መግለጫ ሰጥተዋል ።

በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ሚንስትር ክብርት ዴኤታ ሁሪያ አሊ በወቅቱ እንደገለፁት ፤ የአረጋውያንን ጤንነት እና ደህንነት ለማረጋገጥ እንዲቻል ሳውዲ በቀል በሆነው አልባሳር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን የአይን ህክምና ማዕከል በያሲን ፋውንዴሽን አስተባባሪነት ከሚኒስቴር መ/ቤታችን ጋር በመሆን የአረጋዊያን እና ድሃና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የጤና ችግር ለመቅረፍ በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት እና ቦታዎች የአይን ምርመራና ህክምና አገልግሎቶችን በመስጠት በርካታ አረጋዊያንና ደሃና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደተቻለ ገልፀዋል ።

ከዚህ በፊት በነበሩ ግዚያት በሀገሪቱ ለበርካታ አረጋውያን ዜጎች በኦፒዲ ፣ በአይን ቀዶ ጥገና ፣ በሌንስ እና በመነጽር አገልግሎቶችን በየዓመቱ ሲሰጥ ቆይቷል።

በዘንድሮ ዓመትም በሱማሌ፤ በአፋር፤ በትግራይ እና ሌሎች አከባቢዎች በዓይን ሞራ ቀዶ ህክምና፤ የመነፅር ድጋፍ እና ሌሎች አገልግሎቶች ይሰጣሉ ሲሉ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ጥናት በማድረግ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥቦቸውን ቦታዎች የሚመርጥ ሲሆን፤ የህክምና አገልግሎቱን የሚሰጠው በአልባሳር ዓለም አቀፍ ፋውንዴሽን ሙሉ በሙሉ በነፃ መሆኑ ተገልጿል።

Please follow and like us: