“አሁን ያለውም ሆነ አዲሱ ትውልድ በአንድነትና መተባበር፣ ጥልቅ በሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት በመነሳሳት ታሪኩን ጠብቆ፤ ሀገርን አጽንቶ የማዝለቅ ታሪካዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል” – ክብርት ሁሪያ አሊ

የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አሠራሮችና ሠራተኞች “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል!” በሚል መሪ ቃል 128ኛውን የአድዋ ድል በዓልን በውይይት አከበሩ።

በውይይቱ ወቅትም፥ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ክብርት ሁሪያ አሊ የዓድዋ ድል ጀግኖች ኢትዮጵያውያን በብሔራዊ የአርበኝነት ስሜት የማይቻል የሚመስለውን ወራሪ ሀይል ፊት ለፊት ተፋልመው የተቀዳጁት አንፀባራቂ ድል ነው ብለዋል።

 

ድሉ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ችቦ እና ዓርማ በመሆን ከአውሮፓውያን ቅኝ ግዛት ነፃ እንዲወጡ አስችሏቸዋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የዓድዋ ድል የአሸናፊነታችን ምሥጢር መተባበራችንና አንድነታችን መሆኑን ቅድመ አያቶቻችን በድርጊት ያሳዩንና ያስተማሩን እውነታ እንደሆነም አስገንዝበዋል።

ዘንድሮ ለድሉ የሚመጥን፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክር፣ አሰባሰቢ ታሪክ ያለውና የላቀ ክብር የተንጸባረቀበት ዘመን ተሻጋሪ መታሰቢያ መገንባቱ ለሁላችንም ትላቅ ኩራት ነው ብለዋል። አስበው ተግባራዊ አድርገው ላሳዩትም ምስጋና ችረዋል።

ሆኖም ለህብረ- ብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሰላማችንና ድህነትን ለማሸነፍ ለምናደርገው ጥረት እንቅፋት የሆኑትን ውስጣዊና ውጪያዊ ፈተናዎችን መታገል እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል ብለዋል።

በመሆኑም አሁን ያለውም ሆነ አዲሱ ትውልድ በአንድነትና መተባበር፣ ጥልቅ በሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት በመነሳሳት ታሪኩን ጠብቆ፤ ሀገርን አጽንቶ የማዝለቅ ታሪካዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ሚኒስትር ዴኤታዋ በአጽዕኖት አሳስበዋል፡፡

በዕለቱ የአድዋ ድል በዓልን የተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

Please follow and like us: