ፍልሰትንና ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ተቋማት እንዲደግፉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ።

ፍልሰትንና ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ለመከላከል ባለፉት ስድስት ወራት በግንዛቤ ፈጠራ የስራና የተከናወኑ ተግባራት ምልከታ ተካሂዷል።

የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ዜጎች በየጊዜው በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሲወጡ በድበር ጠባቂዎችና ሌሎች የተደራጁ አካላት እጅ እየወደቁ ከፍተኛ ለሆነ የጤና፣ የስነ-ልቦና፣ የአካል ጉዳት፣ የወሲባዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።

 

 

ይህንን ለመከላከል መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል የተለያዩ ተቋማትን ያቀፈ የግንዛቤ ፈጠራ የስራ ቡድን በአዋጅ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱንና ባለፉት ስድስት ወራትም የተለያዩ ተግባራት በቅንጅት ሲያከናወን መቆየቱን አብራርተዋል።

 

የጥምረቱ አባል ተቋማት በቀጣይ ፍልሰትንና ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና የተጎጂዎችን ሰብአዊ መብት ለማስከበር በሚደረገው አገራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የተቀናጀ አገልግሎት እንዲሰጡና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት የወንጀል ድርጊት መሆኑንና አስከፊነቱን ለህብረተሰቡ ለማስገንዘብ፣ ተጎጂ የሆኑ ተመላሽ ዜጎችን ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ ለመስጠት እንዲሁም ፍልሰትን የተመለከተ ሀገራዊ መረጃ ለማደራጀት እየሰራ ነው።

Please follow and like us: