የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እያካሄዱት ያለው የሱፐርቪዥን ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ አመራሮች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እያካሄዱት ያለው የሱፐርቪዥን ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ የተመራ የሱፐርቪዥን ቡድኑ  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተመረጡ

ክፍለ ከተሞች ላይ፣ የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በሱማሌ ክልል እንዲሁም የሴቶችና ማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ በአፋር ክልል እያካሄዱት ያለው የሱፐርቪዥን ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

 

የሱፐርቪዥን ቡድኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በተለያዩ ዘርፎች የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ ሪፖርት አድምጧል።

ከሪፖርት ባሻገርም በተመረጡ ዘርፎችና አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የመስክ ምልከታ እያካሄደ ይገኛል።

ዘጋቢ መላኩ ባዩ

Please follow and like us: