ሴቶች በፋይናንስ አመራርነት ላይ የሚኖራቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ባለሙያ ሴቶች ኔትዎርክ (ኒውፊን) በይፋ ተመሠረተ።

ሴቶች የፋይናንስ ተጠቃሚነታቸው እንዲጨምርና በአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ላይወደ አመራር እንዲመጡ ብሎም አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ ለማስቻል አስተዋጽኦ የሚያደርግ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ባለሙያ ሴቶች ኔትዎርክ (ኒውፊን) በይፋ ተመሠረተ።

በዕለቱ የክብር እንግዳና የፓናል ውይይት ተሳታፊ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በወንዶችና በሴቶች መካከል ያለው የተሳትፎና የተጠቃሚነት ድርሻ  ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሠፋ መምጣቱን ተናግረዋል።

በአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ላይ ሴቶችን በአመራር ደረጃ የሚኖራቸውን ቦታና አስተዋፅኦ ለማሳደግ እንዲሁም በዘርፉ የሚታየውን የፆታ ተሳትፎ ልዩነት ለማጥበብና ባጠቃላይም በአገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት ላይ የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ አመቺ ምህዳር ለመፍጠር ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተለያዮ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል ።

ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር የብድር አገልግሎት ማመቻቸት ፣ የንግድ ስራ ክህሎትና የቁጠባ ባህል እንዲዳብር የሚያስችሉ ስልጠናዎች እየተሰጡ ስለመሆናቸው የተናገሩት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ የኔትዎርኩ (ኒውፊን) መመሥረት በአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ላይ ሴቶችን በአመራር ደረጃ የሚኖራቸውን ሥፍራና ሚና ለማሳደግ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኔትዎርኩ (ኒውፊን) እንዲመሠረት ያደረገው ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ሲሆን፣ኔትዎርኩ በአፍሪካ ውስጥ ቀደም ብሎ ሩዋንዳ ላይ ከተቋቋመው ተመሳሳይ ኔትዎርክ ልምድና ተሞክሮ በመውሰድ አብሮ ለመሥራት መዘጋጀቱ ታውቋል።

Please follow and like us: