የሕዳሴ ግድባችን በተባበረ ክንዳችን ተሰርቶ እንዲጠናቀቅና የልማት ጉዟችንም እንዲፋጠን የተቋሙ ሰራተኞችን ጨምሮ ሁሉም የዜግነት አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ ቀረበ

የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት የተጣለበት 13ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች አከበሩ።

በክብረ በዓሉ ላይ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስትር አማካሪ ክቡር አቶ ጌታቸው በዳኔ ባለፉት 12 ዓመታት ለግድቡ ግንባታ ሁሉም ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጉልበት፣ በእውቀት፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በአረንጓዴ አሻራና በሌሎችም ዘርፎች ትብብርና ድጋፍ አድርገዋል፤ የዜግነት ድርሻቸውንም ሲወጡ ቆይተዋል ብለዋል።

ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ ዓለም-አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ “የሴቶች ቁጠባ ባህል ለህዳሴያችን ዕድገት መሰረት ነው!” እንዲሁም “ጊዜ የለንም እንሮጣለን! ለህዳሴ ግድባችን እንቆጥባለን!” በሚል መሪ ቃል በ2006 እና በ2009 ዓ.ም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሩጫ እንዲካሄድ ማድረጉንና ይህንንም ተከትሎ ሴቶች በከፍተኛ ደረጃ ቁጠባ ማካሄድ መቻላቸውን አስታውሰዋል፡፡ እንደመንግስት ሠራተኛም ሆነ እንደዜጋ ላበረከቱት አስተዋጽዖ ኢትዮጵያ ታመሰግናቸሁለች ብለዋል። “እንደ ጀመርነው እንጨርሳዋለን!” ብለን ተነስተን ለፈተናዎች ሳንበረከክ “በኅብረት ችለን” አፋፉ ላይ ደርሰናልና አሁንም “የጀመርነውን ዳር ሳናደርስ የሚዝል ክንድ እንደሌለን በተጨባጭ ማሳየት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናገረዋል።

ግድባችን የዓድዋ ድላችን መዘከሪያ፣ የነገው ትውልዳችን መኩሪያም ጭምር ነውና ዛሬም እንደዚህቀደሙ በተባበረ ክንዳችን ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ፤ የልማት ጉዟችንም እንዲፋጠን የተቋሙ ሰራተኞችን ጨምሮ ሁሉም የዜግነት አሻራውን እንዲያሳርፍ ሀገራዊ ጥሪ አቅርበዋል።

 

Please follow and like us: