የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመላው የእስልምና ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

የኢድ በዓል የሰላም፣ የደስታና የአብሮነት ማሳያ እንደመሆኑ እለቱ ሲከብር በመተዛዘን፣ በመደጋገፍና የተቸገሩ ወገኖች በማገዝ ሊሆን ይገባል።

በረመዳን ወር የታየው መረዳዳትና መልካም ስነ ምግባር ከረመዳን በኋላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል።

በዓሉ የሰላም፣ የደስታና የአብሮነት ይሁን!

ዒድ ሙባረክ!

Please follow and like us: