የሰመራ – ሎጊያ ወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥን የተመለከተ የስራ ጉብኝት ተካሄደ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የሰመራ – ሎጊያ ወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከልን ጎብኝተዋል።

ማዕከሉ በአፋር ክልል ከሚገኙ ስምንት የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት መካከል አንዱ ሲሆን ማዕከሉ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት ለማወቅ ተችሏል።ስለሆነም የአካባቢው ወጣቶች በስፋት ወደ  ማዕከሉ እነዲመጡና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የአድቮኬሲ ስራ ተጠናክሮ መሰራት እንዳለበት በጉብኝቱ ወቅት ተመላክቷል።

የአፋር ክልል ወጣቶች ምክር ቤት ምስረታ በትናንትናው ዕለት በሰመራ ከተማ መካሄዱ ይታወሳል።

 

Please follow and like us: