1 ሺህ 234 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 234 ኢትዮጵያውያንን  ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል::

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 234 ዜጎች ሁሉም ወንዶች  ሲሆኑ 26  እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ5500 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: