መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመቀነስ ሚኒስቴር መ/ቤቱ፣ የአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅትና የሰመራ ዩኒቨርስቲ በቅንጅት ለመስራት ተስማሙ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን መቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከሰመራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሞሃመድ ኡስማን እና ከዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱም ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፥ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተለይም ከአማራና ከትግራይ ክልል በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችና ደላሎች አማካኝነት አፋርን እንደመተላለፊያ ኮሪደር በመጠቀም ወደ ጂቡቲና የመን በመጨረሻም መዳረሻቸውን ሳውዲ አረቢያ የሚያደርጉ ወጣቶች፣ ሴቶችና ህጻናት ቁጥር ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ የመከላከል እርምጃ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም በሰመራ ዩኒቨርስቲ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ለመቀነስ የሚያስችል የጥናትና የምርምር ክፍል ለመክፈት ዝግጅት መጀመሩን ተናግረዋል።

የክፍሉ መቋቋም ለህግና ለፖሊሲ አውጪዎች እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቀት ያለው የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለማካሄድ የበኩሉን እገዛ ያደርጋልም ብለዋል። የጥናትና ምርምር ክፍሉን ለማቋቋምና ተፈጻሚ ለማድረግ እንዲረዳ በተዘጋጀው መነሻ ጽሁፍ (concept note) ላይ ሰፊ ውይይት በማካሄድ በጥናትና ምርምር ክፍሉ መቋቋም ላይ የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን በቀጣይ ፍሰተኞች መነሻ ከሆኑበት አካባቢ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በቅንጅት መሰራት እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

Please follow and like us: