የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስቴር እና የፍትህ ሚኒስቴር የ2017 የበጀት ሰሚ መርሀ-ግብር ተካሄደ

የ2017 የበጀት ስሚ መርሀ-ግብር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስቴር እና የፍትህ ሚኒስቴር ከነተጠሪዎቻቸው የ2017 የበጀት ዕቅዳቸውን ለገንዘብ ሚኒስቴር አቅርበው ግምገማ ተካሂዶባቸዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ የዛሬውን የበጀት ስሚ መርሀ-ግብር ሲከፍቱ በጀት የፖሊሲ ማስፈጸሚያ ዋና መሳሪያ መሆኑን ገልፀው ለሚኒስቴሩ የሚቀርቡ ረቂቅ የበጀት ጥያቄዎች የአስር አመቱ መሪ ሀገራዊ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016-2018 የልማትና የኢንቨስትመንት ዕቅድ ግቦችን ከማስፈጸም አኳያ የተቃኘ ሊሆን ይገባዋል ብለዋል።

በዚሁ መሰረትም ሶስቱ ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቶች እና ተጠሪዎቻቸው የ2017 ረቂቅ የበጀት ዕቅዳቸውን በቅደም ተከተል ያቀረቡ ሲሆን በእያንዳንዳቸው ላይ ዝርዝር ግምገማ ከተካሄደባቸው በኋላ ከሚኒስቴሩ የተለያዩ የሰራ ክፍሎች ሙያዊ አስተያየቶች ተሰቷቸዋል።

ባለበጀት መስሪያ ቤቶችም የቀረቡላቸውን ዝርዝር አስተያየቶች በግብአትነት አካተው በተቀመጠው ጣራ መሰረት ቁጠባና ውጤታማነትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተከለሰ ዕቅዳቸውን በሶስት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ አቅጣጫ መሠጠቱን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Please follow and like us: