የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም እንደ አገር የተነደፉት ስትራቴጂዎች፣ ፕሮግራሞችና የድርጊት መርሀ ግብሮች ተፈጻሚ እንዲሆኑና ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም አካላት በተቀናጀ አግባብ እንዲሠሩ ተጠየቀ

ይህ የተገለፀው በሀገራችን ገጠራማው ክፍልና በከተሞች ውስጥ ራሳቸውን መመገብ ለማይችሉና ህልውናቸው አደጋ ወስጥ ለወደቁ የህብረተሰብ ክፍሎች በገጠርና ከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም እንደ አገር የተነደፉት ስትራቴጂዎች፣ ፕሮግራሞችና የድርጊት መርሀ ግብሮች ተፈጻሚ እንዲሆኑና ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል ለባለድርሻና ፈፃሚ አካላት በተዘጋጀው መድረክ ላይ ነው።

በዕለቱ የመክፈቻ ንግግርና መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ጥበቃ፣ ማስተባበሪያና መከታተያ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋዬ ሽፈራው እንደገለፁት የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ዜጎች ወደ ዘላቂ ህይወት እንዲሸጋገሩና የማህበራዊ ደህንነታቸው እንዲረጋገጥ የሚያስችሉ ልማት ተኮር ፕሮግራሞች አፈጻጸምና ስኬታማነት ለማሳደግ እርምጃዎችን በመውሰድ ያለሳለሰ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል ።

አቶ ተስፋዬ እንደገለፁት አጠቃላይ የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በሚተገበርባቸው የሀገራችን ገጠርና ከተሞች ላይ ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ ለሚደርገው ጥረትና ስኬታማነት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ወደፊትም ድጋፉን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በስልጠናው በገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ላይ ለሚሠሩ ባለድርሻ አካላት በአካባቢያዊና ማህበራዊ ማስፈፀሚያ (Environmental & Social Commitment Plan) ላይ የስርዓተ ፆታና የፆታዊ ጥቃት መከላከል፣ የማህበራዊ ጤና መድህን አገልግሎት ትስስር፣ የማህበራዊ ጥበቃ ማዕቀፍ፣ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ መከላከል፣የቅድመ ልጅነት ዘመን ዕድገት ማዕከላት ግንባታና አስተዳደር እና የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት መመሪያዎች ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።

በተጨማሪም በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ላሉ ባለድርሻ አካላት በፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ በማህበራዊ ስነልቦናዊ ድጋፍ፣ በዳታ ማኔጅመንት ፣በህይወት ክህሎት፣ በመሰረታዊ ማህበራዊ አገልግሎት አሰጣጥና ሪፈራል ሊንኬጅ እንዲሁም የማህበረሰብ አቀፍ ጥምረቶች ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ባላቸው ጠቀሜታ ዙሪያ ስልጠና በመስጠት ተሳታፊዎች በእውቀትና በክህሎት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ማሳለፍ የሚችሉበትን አቅም በመገንባት የፕሮግራሙን አፈፃፀም ማሻሻል ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል ።

Please follow and like us: