1 ሺህ 175 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሱ

በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 175 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 175 ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 18 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊ ህጻናት ይገኙበታል።ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ27ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

Please follow and like us: