የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአውስትራሊያ መንግስት በትብብር የሚሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችላቸውን ውይይት አደረጉ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአውስትራሊያ መንግስት በጋራ በስርዓተ-ፆታ እኩልነት ሴቶች ማብቃት፣ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ የሚሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችላቸውን ውይይት አደረጉ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት የአውስትራሊያ መንግስትና ኢትዩጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ወዳጅነት ያላቸው ሀገሮች እንደሆኑ ገልፀዋል ። ሚኒስትሯ እንደገለፁት የአውስትራሊያ መንግስት ለሚኒስትር መስሪያቤቱ እስከዛሬው ላደረገው አስተዋጾ አመስግነው በቀጣይ በሁሉም ደረጃዎች የሴቶችን አመራር ተሳትፎ ማሳደግ ፣ሴቶች በሰላም ግንባታ ሂደት ማሳተፍ፣ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳደግ፣ ፣የስርዓተ-ፆታ እኩልነትንና ፣ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ የሚሰጠውን ድጋፍ እና ምላሽን ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ማረጋገጥ ላይ በጋራ ለመስራት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለ CEDAW( the Committee on the Elimination of Discrimination against Women)2025-2028 በድጋሚ ለመመረጥ የአውስትራሊያ እጩ፣ ወይዘሮ ናታሻ ስቶት ዴስፖጃ
በበኩላቸው አውስትራሊያ በጾታ እኩልነት እና በሴቶች ማብቃት ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ መሪ ለመሆን እንደምትሰራ አሰሰታውቀዋል። አክለውም ኢትዮጵያ በስርአት ፆታ እኩልነትና በሽግግር ፍትህ ረገድ ያስመዘገበችው ውጤት የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም ከኢትዮጵያና ሚኒስትር መስሪያቤቱ ጋር በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

Please follow and like us: