ከተረጂነት መንፈስ ተላቆ ጠንክሮ በመስራት ለመጭው ትውልድ ምንዳን ማውረስ እንደሚገባ ተገለጸ

ከተረጂነት መንፈስ ተላቆ ጠንክሮ በመስራት ለመጭው ትውልድ ምንዳን ማውረስ እንደሚገባ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገለጹ። በሀረሪ ክልል “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር” በሚል ህዝባዊ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

ህዝባዊ የምክክር መድረኩን የመሩት የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከተረጂነት መንፈስ ተላቆ ጠንክሮ በመስራት ለመጭው ትውልድ ምንዳን በማውረስ የይቻላል መንፈስን መላበስ እንደሚገባ ገልፀዋል። በእርዳታ ያደገ አገር የለም ያሉት ሚኒስትሯ የስራ ባህልን በመቀየር ከተረጂነት ለመውጣት የሚያስችሉ እድሎችን አሟጦ በመጠቀም ምርታማነትን በማሳደግ ተረጅነትን መፀየፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ይህን እውን ለማድረግም ሀረር የምትታወቅበትን  እርስ በእርስ የመረዳዳት እሴት ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አቶ ታንኳይ ጆክ በበኩላቸው አርሶ አደሩ በጉልበቱ ሰርቶ ውሃ በማቆር እያከናወነው የሚገኘውን የአታክልት ልማት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብዋል። በሌማት ትሩፋት ዘርፍም በንብ ማነብ እና ከብት እርባታ ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን ግለታቸውን ጠብቀው እንዲሄዱ እየተደረገ የሚገኘውን ድጋፍ እና እገዛ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል ። በሌላ በኩል ተግባራዊ በተደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ደርቆ የነበረው የሀሮማያ ሀይቅ ሊያገግም መቻሉን በመጠቆም የአረንጓዴ አሻራ በክልሉ ብሎም አካባቢው አየር ንብረት ላይ ለውጥ ከማምጣት ባሻገር ምርታማነትን መጨመሩን አመላክተዋል።

የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተጀመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክረው በማስቀጠል ከተረጂነት በመውጣት የአገሪቱን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ገልፀዋል። በውይይቱ ላይ የተረጂነት አስተሳሰብ በግልም ሆነ በአገር  ላይ የሚያደርሰው ጉዳትና መፍትሄዎቹ ላይ ውይይት በማድረግ ጠንክሮ በመስራት ሁሉም ሚናውን ለመወጣት ስምምነት ላይ ተደርሷል ሲል የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

 

Please follow and like us: