1 ሺህ 132 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 132 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 132 ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 6 ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

Please follow and like us: