“የበጎ ፍቀድ አገልግሎት በተደመረ ጉልበት፣ እውቀትና ክህሎት ሀገር የመገንባት ሂደት ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

የ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረከ  “በጎነት እና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ !!!“ በሚል መሪ ቃል ይከናወናል።

በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ተመስገን ጥሩነህ እንደገለጹት ፤ የበጎ ፍቀድ አገልግሎት በተደመረ ጉልበት፣እዉቀትና ክህሎት ሀገር የመገንባት ሂደት ነዉ ። ከዚህ ቀደም በበጎ ፍቃድ በተሰጡ አገልግሎቶች የማህበረሰቡ አንገብጋቢ ችግሮች መፈታት ተችሏል። በዘንድሮዉ ክረምትም ሚሊዮኖች ይደገፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር  ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) በበኩላቸው ዜጎች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት ላይ በንቃት ተሳትፈው እራሳቸውንና ማህበረሰባቸውን ሊጠቅሙ የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት እንደሚገባ መንግስት እና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አምኖ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል ። ለዚህም የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በተቀናጀ አግባብ ለመምራትና ዜጎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ባህል ማድረግ እንዲችሉ የኢትዮጵያ የተለያዩ ፓሊሲዎችን እና አሰራር ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ የፓሊሲ ዝግጅት ረቂቅ ተዘጋጅቶ ለሚመለከተው የመንግስት አካል የቀረበ ሲሆን፤ ለዚህ ጋር ተያይዞ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ስታንዳርድ ተቀርጸው ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል ።

በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር  ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም፣ የክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደሮች፣ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሲቪክ ማህበረሰብ አመራሮች ተገኝተዋል።

በ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የስምሪት መርሐ-ግብር 34,274,197 በጎ ፈቃደኞችን በ14 የስምሪት መስኮች በማሰማራት 49,598,406 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ 26,051,064,875 ብር የሚገመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት፣ ማህበራዊ ትስስር እና ህብረ ብሔራዊ አንድነት የሚጠናከርበት እንደሚሆን በመድረኩ ተገልጿል ።

 

Please follow and like us: