እስካሁን ከ49 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ49 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለትም በ3 ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 175 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ዛሬ ወደ ሀገር የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 20 ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

 

Please follow and like us: