ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራው በታቀደው መሰረት እንደቀጠለ ይገኛል እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ ኢትዮያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራው በታቀደው መሰረት የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት ብቻ በ3 ዙር በተከናወነ በረራ 1ሺህ 173 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

ዛሬ ወደ ሀገር የተመለሱት 1ሺህ 173 ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 17 ታዳጊዎች ይገኙበታል። በሳውዲ አረቢያ በተለያየ ማቆያ ጣቢያ የሚገኙ 70 ሺህ ኢትዮጽያዊያንን ወደ ሀገር ለመመለስ በእቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል። ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ ሀገር ለመመለስ በተደረገው ጥረት እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል። ለተመላሽ ዜጎችም በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ እየተደረገና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራው በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

 

Please follow and like us: