1 ሺህ 169 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

(አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22/ 2016 ዓ.ም) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 169 ኢትዮጵያውያን በዛሬው እለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገር የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 1 ጨቅላ ህፃናን እና 30 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢው ድጋፍ እና እንክብካቤ እየተደረገና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ52 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

Please follow and like us: