“ለብቻ ፣የእኔ ከሚለው እኛ የሚል አስተሳሰብን መፍጠር አለብን”። ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

ይህ የተገለፀው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር በዘለላ 10 የፖሊሲ አድቮኬሲ እና ኔትዎርኪንግ ኢቨንት በStartup Ethiopia Policy Actions (Toward Youth Economic Empowerment) መድረክ ላይ ነው።

ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር እንደገለፁት “ለብቻ ፣የእኔ ከሚለው እኛ የሚል አስተሳሰብን መፍጠር አለብን”።ብለዋል ለብቻ የሚጮህ ድምፅ አይሰማም፣ወጣቶች ድምፃቸውን ለማሰማት እርስ በርስ በጋራ መቆም አለባቸውም ብለዋል። ሚኒስትሯ እንደገለፁት ለሀሳብ ቦታ ካልሰጠን በቀር ገንዘብ ብቻ መስጠት ብቻውን ውጤት እንደማያስገኝ ከዚህ በፊት ከነበረን ልምድ አይተነዋል።

ወጣቶች በአገሪቱ ልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ የተቀረጹ ፖሊሲዎች፤ እስትራቴጆች ፤ፕሮግራሞች ፤መርሀ-ግብሮች ከተግባራቸው ጋር ተጣጥመው እንዲሄዱና ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል አዳዲስ ፖሊሲዎችን ከመቅረፅ እስከ ማሻሻል ሚኒስቴር መስሪያቤቱ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የወጣቶችን አመለካከት ለመለወጥና የስራ ባህላቸዉን ለማሳደግ ከሚያከናዉናቸዉ ተግባራት ጎን ለጎን የጀማሪ ስታርት አፕ ወጣቶችን የፋይናንስ ችግሮች በመፍታት ዙሪያ አጽንኦት ሰጥቶ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል ።

የኢትየጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወይዘሪት ሳሚያ አብዱልቃድር በበኩላቸዉ ማህበሩ ስራ ፈጠራን ለማስተዋወቅ፣ ለመደገፍ፣ ወጣቶች ራዕያቸውን ዕውን የሚያደርጉበት ምቹ ስነምህዳር እንዲፈጠር በወጣት ስራ ፈጣሪዎች እ.አ.አ በ2020 መቋቋሙን አስታውሰዋል። ማህበሩ ከሀገር ውስጥም ውጭም ካሉ መንግስታዊ፣መንግስታዊ ካልሆኑ፣ የልማት አጋር ተቋማት እና ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል ።

በዕለቱ የፓናል ውይይትና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትየጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

 

Please follow and like us: