ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ዜጎች ቁጥር ከ55 ሺህ በላይ ተሻግሯል

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጋ ተኮር የዲፕሎማሲ ስራ ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ዜጎች ቁጥር ከ55 ሺህ በላይ ተሻግሯል።

በዛሬው እለት ብቻ በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 178 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል። ዛሬ ወደ ሀገር የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 14 ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በሳዑዲ ዓረቢያ በተለያየ ማቆያ ጣቢያ የሚገኙ 70 ሺህ ኢትዮጽያዊያንን ወደ ሀገር ለመመለስ በእቅድ ተይዞ ለስኬታማነቱ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል።

 

Please follow and like us: