1 ሺህ 148 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

(አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29/ 2016 ዓ.ም) በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 148 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገር ከተመለሱት 1 ሺህ 148 ዜጎች ውስጥ 1143 ወንዶች፣ 5 ሴቶች ሲሆኑ ከነዚህም መካከል 128 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ57 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: