1 ሺህ 198 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 198 ኢትዮጵያውያን በዛሬው እለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገር የተመለሱት ዜጎች 1ሺህ 041 ወንዶች፣ 134 ሴቶች እና 23 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 31 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ63 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: