በኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የተመራው ልዑክ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑካኑ በአዲስ አበባ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስም በተቋሙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና ልዑካቸው በኒውዮርክ ተዘጋጅቶ በነበረው የተባበሩት መንግስታት የስነ ህዝብ ድርጅት የ2024 አለም አቀፍ የእውቅና መርሀ ግብር ላይ ኢትዮጵያን በመወከል መሳተፋቸው ይታወሳል። በዚህ መርሃ ግብርም ኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት ለመከላከል በሰራችው ስራ እውቅና ማገኘቷ ይታወቃል።

ወጤቱ እንደሀገር መንግስት በወሰደው ጠንካራ እርምጃ፣ በየደረጃው በተደረገ ከፍተኛ ጥረት እንዲሁም በተሰራ ሰፋፊ የግንዛቤና የንቅናቄ ስራ የተገኘና የሁሉም አካላት ርብርብ ድምር ውጤት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በድጋሚ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላልፋል። በቀጣይ በሴቶችና ህጻናት ላይ አካላዊ፣ አእምሯዊ፣ ስነልቦናዊና ሌሎች ጉዳት የሚስከትሉ ጥቃቶችንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለማስቆም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል።

Please follow and like us: