የበጎነትና አብሮነት አሻራ – በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ

(ጅግጅጋ፣ ሐምሌ 9/ 2016 ዓ.ም) በወሰን ተሻጋሪ የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ወጣቶች በሱማሌ ክልል የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን አከናውነዋል።

 

የወሰን ተሻጋሪ ወጣት በጎ ፍቃደኞች ሸበሌ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ መሀዲን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ወጣቶች አቀባበል አደርገውላቸዋል። በዚህ ወቅት ወጣቶች አንድነታቸውንና አብሮነታቸውን ይበልጥ ማጎልበት እና በየአካባቢው የተጀመሩ የበጎ ፈቃድ ስራዎችንም ወደፊትም አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል።

ወጣቶቹ በክልሉ በነበራቸው ቆይታም የደም ልገሳ እና ችግኝ ተከላ በጎ ፍቃድ ስራዎችን በማከነወን ማህበረሰቡን የማነቃቃት ስራ ሰርተዋል።

Please follow and like us: