የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች ከተባበሩት መንግስታት ተቋማት ጋር በትብብር መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የሴቶችና ህጻናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ

የተባበሩት መንግስታት ረዳት ሴክሬተሪ ጀነራል እና በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ ዶ/ር ራሚዝ አልካባሮቭ እና በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የስነህዝብ ፈንድ ፕሮግራም ተወካይ ሚስተር ታይዎ ኦሉዮሚን ተቀብለው አነጋግረዋል። በዚሁ ጊዜም የስራ ኃላፊዎቹ በዋናነት ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን መከላከል እና የስርዓተ ጾታ እኩልነትን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ አብሮ ለመስራት በሰፊው ተወያይተዋል።

በተጨማሪም ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በተለይም ደግሞ ያለዕድሜ ጋብቻንና የሴት ልጅ ግርዛትን ለመከላከል እንዲሁም ሴት ወጣቶችን በኢኮኖሚ ለማብቃት የሚያግዙ ስራዎችን በጋራ መስራት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂደዋል። በተነሱ አጀንዳዎች ዙሪያ በቀጣይ ከሚመለከታቸው አለም አቀፍ ተቋማት በጋራ ለመምከርና መግባባት ላይ ለመድረስ የሚያስችል ውይይት እንደሚካሄድ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል።

 

Please follow and like us: