የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤመሬቶች ወጣቶች ግንኙነት የሚያጠናክር ምክክር ተካሄደ

በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤመሬቶች ወጣቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ተካሄደ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የወጣቶች ሚኒስትር ሱልጣን አልኒያዲ ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤመሬቶች ወጣቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል። በትምህርት፤ በስፔስ ሳይንስና በቴክኖሎጂ ዙሪያ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

ከዚህም ባሻገር በወጣት ለወጣት ግንኙነትና ልምድ ልውውጥ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል። በትናንትናው ዕለት በኢትዮዽያና እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ይፋ በተደረገው የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ የዲጂታል ሥራ ክሂሎቶች ማሳደጊያ የትብብር ፕሮጀክት ላይም በትብብር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ከብሪክስ የወጣቶች ጉባኤ ጎን ለጎን ከብሪክስ አባል አገራት የወጣት ሚኒስትሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እያደረጉ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።

 

Please follow and like us: