በዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ሲኒየር የፕሮግራም ስራ አስኪያጅና የፕሮቴክሽን ዩኒት ሃላፊ ለሆኑት ወሪ/ት ሣራ ባሻ የሽኝት ፕሮግራምና የእውቅና ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ወ/ሪት ሳራ ባሻ በዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ውስጥ በነበራቸው ሃላፊነት

ሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሲያካሂዳቸው በነበሩ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን በመከላከል፣ ለተመላሽ ዜጎች በሚደረገው መልሶ ማቋቋምና ጥበቃ፣ የፍልሰት መረጃን በማደራጀት ረገድ ለተመዘገቡ ውጤታማ ስራዎች በሙያ፣ ቴክኒክና በቁሳቁስ እንዲሁም ለፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚሆኑ ሀብቶችን በማሰባሰብ ረገድ ከፍተኛ እገዛ በማድረግ፣ በተለይም በዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅትና በሚኒስቴር መስሪያቤቱ መካከል ያለው የስራ ግንኙነት ላቅ ወዳለ ደረጃ እንዲሸጋገር ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ወ/ት ሣራ ባሻ በተመደቡበት በከፍተኛ የስራ ሃላፊነት ጄኔቫ የሚገኘው የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ጽ/ቤት የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ እንዲሰሩ ሚኒስትሯ አደራቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

Please follow and like us: