የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን በቦታው በመገኘት አፅናንተዋል

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ዞን በተከሰተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖችን በስፍራው በመገኘት ጎብኝተዋል፤ ተጎጂዎችንም አፅናንተዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዚሁ ጊዜም የተከሠተው ድንገተኛ አደጋ ያደረሠው ጉዳት ልብ የሚሰብር መሆኑን ገልፀዋል። “በደረሠው አደጋ ምንም እንኳን ቤተሰቦቻችሁን ያጣችሁ ቢሆንም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችሁ አለን” ሲሉ ተጎጂዎችን አፅናንተዋል። በቀጣይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሁኔታውን እንደሚከታተል እንዲሁም በአደጋው ለተጎዱ ወገኖችም ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበርና በማስተባበር አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ እንደሚደርግ አስታውቀዋል።

Please follow and like us: