የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የቻይና ፋውንዴሽን ፎር ሩራል ዴቨሎፕመንት በተለያዩ መስኮች በትብብር መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ::

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የቻይና ፋውንዴሽን ፎር ሩራል ዴቨሎፕመንት በ2ኛው ምዕራፍ የትብብር ማዕቀፍ በ7 ዋና ዋና የልማት መስኮች ደሀና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ፕሮጀክት ተፈራርሟል።

በመርሃ -ግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለፁት፥ ኢትዮጵያና ቻይና በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፍ ለአመታት የዘለቀ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዋል። የቻይና ፋውንዴሽን ፎፍ ሩራል ዴቨሎፕመንትም የዚሁ ዘመናትን የተሻገረ የእርስ በርስ ጠንካራ ወዳጅነትና ትብብር ተምሳሌት አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል። እነዚህም ፕሮጀክቶች በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለመደገፍ እንደሀገር የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ጠቅሰው፥ ውጤታማ እንዲሆኑም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

 

በመርሐ ግብሩ ላይ የፋውንዴሽኑ ካንትሪ ዳይሬክተር ይን ቼን በበኩላቸው ÷ ፋውንዴሽኑ በተጠቀሱት ዘርፎች አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚ ኮንስለር ሚስተር ያን ይሃን በበኩላቸው÷ ቻይና በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ አስተዋጽኦ እያደረገች ትገኛለች ብለዋል። ፕሮጀክቱ ደሃና ለችግር ተጋላጭ ለሆኑት ህብረተሠብ ክፍሎች አካባቢ የትምህርት ቤት ምገባን ወደ ገጠር ማስፋፋት ፣ለተማሪዎች የሚሰጡ የትምህርት ቁሳቁሶች ፣ በፀሀይ የሚሰሩ ታዳሽ የሀይል ምንጮች ገጠራማና የኤሌክትሪክ አቅርቦት እጥረት ያለባቸው በትምህርት ቤቶች አካባቢ ላይ የንፅህና ማስጠበቂያ ፣ የሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ፣ ንፁህ የመጠጥ ውሀን በትምህርት ቤቶች ማስፋፋት ፣ውሀ አጠር የሆኑ አካባቢዎችን የውሀ ተጠቃሚ ማድረግን ያለመ ነው። እነዚህ ስራዎች ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሌሎች ሚኒስቴር መስሪያቤቶችና ክልሎች ጋር በጋራ የሚሠራ ይሆናል። ፕሮጀክቱ ስምምነቱ ከተደረሰበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል ።

Please follow and like us: