ኢትዮጵያ የሴቶች ሰላምና ደህንነት ላይ ያተኮረ ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብር እንዲኖራት የሚያስችል ግብአት ማሰባሰቢያ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሁሉም የፌደራል ተቋማት ከተወከሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የሴቶች ሰላምና ደህንነት ላይ ያተኮረ በብሔራዊ ደረጃ የሚዘጋጅ የድርጊት መርሃ ግብር የስትራቴጂ ሰነድ ለማዘጋጀት ግብአት በመሰብሰብ ላይ ይገኛል።

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካቶ ትግበራ ማብቃት ዴስክ ኃላፊ አቶ ጌቱ በላይ እንደገለፁት ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብሩን ለማርቀቅና ለማጠናቀቅ የአውድ ዳሰሳ፣ ተቋማዊ ኦዲት፣ የህግ ማዕቀፍ ግምገማ ጥናቶችም መደረጋቸውተጠቅሷል ። በተጨማሪም ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ሰላምና ደህንነት ላይ ባወጣው ወሳኔ 1325 መሠረት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን ጠቅሰዋል ። ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብሩ ኢትዩጵያ በሴቶች፣ የሰላም እና ደህንነት አጀንዳዎች ላይ ከመከላከል፣ጥበቃ ማድረግ፣ ተሳትፎና እፎይታ ማገገም ምሰሶዎች ላይ የምትወስደውን እርምጃ አካባቢያዊ ለማድረግ የሚስችል በብሔራዊ ደረጃ የሚዘጋጅ የሴቶች የሰላምና ደህንነት የድርጊት መርሃ ግብር ነው።

ሰነዱ በግጭት ሁኔታዎች ውስጥ የሴቶች እና ታዳጊ ሴቶች ሰብአዊ መብቶችን ለማስጠበቅ በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራት የሚወስዷቸውን ዓላማዎች እና ተግባራት ይዘረዝራል። በተጨማሪም በሴቶች እና ታዳጊ ሴቶች ላይ የትጥቅ ግጭቶችን እና ጥቃቶችን በመከላከል እና ሴቶች በሰላም እና ደህንነት ላይ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው ሚናቸውን እንዲረጋገጥ የሚያስችል ሰነድ ነው፡፡ በዕለቱ በሴቶች ሰላም እና ደኅንነት ላይ በኢትዮጵያ የተሳካ ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብር ለማዘጋጀት የሚያግዝ የተቋማቱን ኃላፊነት መነሻ በማድረግ ሴቶች ሰላምና ደህንነታቸው በግጭትና በጦርነት ወቅት ለመጠበቅ የሚያስችሉ የተለያዮ ምክረ ሀሳቦች ከተቋማቱ ተወካዮችና የስራ ሂደት ኃላፊዎች ቀርበዋል። ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብሩ ቀደም ሲል በድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር፣ በሀረሪ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎችና በፌዴራል ደረጃ የሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለውይይትና ለምክረ ሀሳብ መቅረቡ ይታወሳል። በቀጣይም ረቂቅ ሰነድን ይፋ ለማድረግ ወደ ተቀሩት ክልሎችና አዲስአበባ ከተማ መስተዳድር እንደሚቀርብ ተገልጿል ። የብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብሩን ተግባራዊ ለማድረግ ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴርበዋናነት የሚያስፈፅም ሲሆን በአጋርነት የተለያዮ ሚኒስቴር መስሪያቤቶች ፣ ፌደራል ፖሊስ ፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የተባበሩት መንግስታት ሴቶች፣ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም፣ የበይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን በዋናነት ይገኙበታል ።

Please follow and like us: