የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች በእንጦጦ ፓርክ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።

(ነሃሴ 17/2016)የምትተከል ሀገር የሚያፀና ትውልድ በሚል መሪ ቃልየአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ዘመቻን በመቀላቀል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች በእንጦጦ ፓርክ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል ። በዛሬው ዕለት ከተተከሉት ችግኞች መካከል ሀገር በቀልና ለአፈር ጥበቃ እና የመሬት መራቆትን ለማስቀረት አስተዋፅዖ የሚያደርጉ እፅዋቶች ተተክለዋል። በዛሬው ሁነት መጨረሻ በመላው ሀገራችን ባለፉት አምስት አመታት የተተከሉ ችግኞች ወደ 40 ቢሊዮን በማድረስ ኢትዮጵያ ሪከርድን በድጋሚ ታሻሽላለች።
Please follow and like us: