የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ተካሄደ

የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ተካሄደ

መርሃ ግብሩን በማስመልከት የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ ለ5 አቅመ ደካሞች የቤት ግንባታ ስራ ዛሬ በዳውሮ ዞን በታርጫ ከተማ በይፋ አስጀምረዋል። የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር GGGI ከተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያስገነባውና ደረጃቸውን የጠበቁ የመኖሪያ ቤቶች ሲጠናቀቁ በውስጣቸው ሙሉ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች እንደሚያሟሉ ተገልጿል።

ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች የሚገነባላቸው ዜጎች የዕድሉ ተጠቃሚዎች መሆን በመቻላቸው በእጅጉ መደሰታቸውን በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል። በተጨማሪም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ 150 ህፃናት ለ2017 በጀት ዓመት የሚሆን ልዩ ልዩ የትምህርት ቁሳቁሰ ድጋፍ ተደርጓል። የፌዴራልና የክልሉ አመራሮች በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ታርጫ ካምፓስ ቅጥር ግቢ በመገኘት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውነዋል።

የአረንጓዴ አሻራ ስራዎችና ሰው ተኮር የበጎ አድራጎት ተግባራት ለማስቀጠል ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። ከተባበርን፣ በአንድነት ቆርጠን ከተነሳንና ከሰራን ልመናን ታሪክ ማድረግ እንችላለን ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት እንደመሆኗ ዜጎችን ከተረጂነት ለማላቀቅ ህዝቡና የክልሉ መንግስት በጋራ እንዲረባረብ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመርሀ ግብሩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸው በለውጡ መንግስት ትልልቅ ተስፋዎችን ወደ ሚጨበጥ ስንቅ እየቀየርን በድል ላይ ድል መጎናፀፍና ሁሉን አካታች ያደረገ የልማት ስራዎች ማካሄድ ተችሏል ብለዋል። በዕለቱ ከዚህ ቀደም በዞኑ አቅም በበጎ ፈቃድ ተገንብተው ለአረጋዊያንና ለአቅመ ደካሞች የተላለፉ የመኖሪያ መንደር ጉብኝት የተደረገ ሲሆን መሰል ሥራዎችን ለማጠናከር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ ተብሏል።

Please follow and like us: