1 ሺህ 254 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

(አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25/ 2016 ዓ.ም) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን ለመመለስ ትናንት ሌሊትና ዛሬ ቀን ላይ በተደረገ በረራ በድምሩ 1 ሺህ 254 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

ወደ ሀገር የተመለሱት 945 ወንዶች፣ 262 ሴቶች፣ 47 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 103 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ76 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: